Ethiotelecom Logo

ላፕቶፕ ስንገዛ ምንምን ነገሮችን ማገናዘብ ይኖርብናል


ላፕቶፕ ስንገዛ ምንምን ነገሮችን ማገናዘብ ይኖርብናል

አዲስ ላፕቶፕ ለመግዛት እያሰቡ ከሆነ, ይህ በጣም ጊዜ የሚወስድ መስሎ ተሰምቶት ይሆናል፡፡ ምን አይነት ላፕቶፕ እየፈለጉ ነዉ በቀላሉ የሚያዝ ኮምፒውተር ፤  በጣም ፈጣን እና የመልቲሚዲያ ስራዎች እንዲቆጣጠሩ የሚያስችልዎት? በጀትዎስ? የተሳሳተ ምርጫ ከራስ ምታት በተጨማሪ አላሰፈላጊ የሆነ ገንዘብ ያስዎጣዎታል፡፡  ይህ በኩራዝ ቴክኖሎጂስ የተዘጋጀ ብሎግ እርሶ እንዴት የተሻለ ኮምፒዉተር መምረጥ እንደሚችሉ አስፈላጊ መረጃ ይሰጥዎታል፡፡

ኮምፒዉተር ሲገዙ ልብ ሊሏቸዉ የሚገቡ ጉዳዮች፡

  1. በጀት

በሃገራችን የኮምፒዉተር ገበያ እጅግ ተለዋዋጭ በመሆኑ የተነሳ ዛሬ እና ነገ የሚኖረዉ ዋጋ ልዩነቶች ይኖሩታል፡፡ ኮምፒዉተሮች በአሁኑ ጊዜ ከአስርሺዎች እስከ መቶሺዎች ባለዉ የብር ምንዛሬ ይሸጣሉ፡፡ ኮምፒዉተሮቹ ከይዘታቸው በተጨማሪ አይነታቸዉ አዲስ (NEW) ፤ በድጋሜ የተሰራ (Refubrished) ፤ የተወሰነ ያገለገለ (Slightly Used) እና ያገለገለ (Used) በመባል ይከፈላሉ፡፡

አዲስ፡ ከፋብሪካ ከወጣ ምንም አይነት አግልግሎት ያልሰጠ

በድጋሜ የተሰራ፡ ኮምፒዉተርሩ ከአገለገለ በኋላ ፋብሪካ ገብቶ ተሻሽሎ የወጣ

የተወሰን ያገለገል፡ ብዙ አገልግሎት ያለሰጡ በተለይ ከዉጪ ሃገር ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ተጠቀመዉ የሸጧቸው ናቸዉ

ያገለገለ፡ በደንብ ጥቅም ላይ የዋለ ባሌቤቱ ሌላ የተሻለ ፈልጎ የሸጠው ወይንም  እና ብልሽት አጋጥሞት ተጠግኖ እንደ አዲስ የሚሸጥ ሊሆን ይችላል፡፡

ዋጋቸዉም እንደቀደምተከተላቸዉ ነው፡፡

2. ፕሮሰስር (ሲፒዩ)

ከሁሉም መሰፈርቶች እጅግ ወሳኙ መስፈርት ነዉ፡፡ ሲፒዩ የኮምፒዉተር አዕምሮ ነው፡፡ ኮምፒዉተር የሚሰራቸዉ ስራዎች የሚያስብለት ፤ ሂሳቦችን የሚያሰላለት ፤ ምላሾችን የሚሰጥለት እና የሚያገናዝብለት ክፍሎ ይህ ፕሮሰሰር ነዉ፡፡

የኮምፒዉተራችን ፍጥነት የሚወስነው ይህ ፕሮሰሰር ነዉ፡፡ የተለያዩ ፕሮሰሰር አምራቾች ቢኖሩም በሃገራችን ገበያ ላይ በአብዛኛዉ የሚገኙት የኢንቴል ፕሮሰሰሮች ናቸዉ፡፡ ኮር አይ 3 ፤ ኮር 5 ፤ ኮር አይ 7 እና ኮር  9  ኮምፒዉተሮች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ ከፍተኛ የሆነ አቅም አላቸዉ ፤ ዋጋቸዉም በክፍተኛ ሁኔታ ይለያያል፡፡  ለአብዛኞቹ ኮምፒዉተሮች የሚመከረዉ ኮር አይ 5 ነዉ፡፡

ከፕሮሰሰር ጋር ተያይዞ የኮምፒዉተሮች ጀነሬሽናቸዉን መመልከት ተገቢ ነዉ፡፡ የጀነሬሽን ልዩነት ራማችንም ላይ የዲዲአር 3 እና ዲዲአሪ 4 ልዩነትን ያመጣል፡፡ ጀኔሬሽኑ በጨመረ ቁጥር ዋጋውም ላይ ከፍተኛ ልዩነቶች ይኖሩታል፡፡

3. ራም

ራም የኮምፒውተር ማስታወሻ መመዝገቢያ ነዉ፡፡ ኮምፒዉተር ብዙ ራም አለዉ ማለት ሲፒዩ ብዙ መረጃዎችን መመዝገብ እና ማስተላለፍ ቻለ ማለት ነዉ፡፡ ይሄም ኮምፒዉተር በቀላሉ ስራዉን እንዲሰራ ያስችለዋል፡፡ በቂ ራም ከሌለን ኮምፒዉተራችን በቂ ሚሞሪ ወይም መመዝገቢያ ስለማይኖረዉ ብዙ ሶፍትዌሮችን በተጠቀምን ቁጥር ኮምፒዉተራችን ዘገምተኛ እየሆን እና ፍጥነቱ እጅግ እየቀነሰ ያስቸግረናል፡፡ ኮምፒዉተር ስንገዛ በትንሹ 4 ጊጋባይት ራም ያስፈልገናል፡፡ የግራፊክስ እና ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት የምንሰራ ከሆን ደግሞ ከ8 ጊጋባይት በላይ ራም ቢኖረን ይመከራል፡፡ ለጌሚንግ እና አርክቴክቸር ሶፍትዌሮች ደግሞ ከ16 ጊጋ ባይት በላይ ራም ያላቸዉ ኮምፒዉተሮችን መግዛት ይመከራል፡፡

4. ባትሪ

ላፕቶፕን ምናልባት ከሲፒዩ እና ራም ጋር ባይወዳደርም አስፈላጊ የሆነ ጉዳይ ነዉ፡፡  በተለይ እንደ ሀገራችን ሁኔታ መብራት አስተማማኝ በማይሆንበት ጊዜ እና ሶኬት ልናገኝባቸው የማንችላቸዉ ቦታዎች ላይ ኮምፒውተራችንን ለመጠቀም እንድንችል አስተማማኝ ባትሪ ሊኖረን ይገባል ስለዚህ የምንገዛዉ ላፕቶፕ ኮምፒዉተር 4 ሰዓት እና ከዚያ በላይ ማገልገል እንደሚችል ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡

5. ሃርድ ዲስክ ድራይቭ

ሃርድ ዲስክ የኮምፒዉተራችን ቋሚ የመረጃ ቋት ነዉ፡፡ ምስሎቻችን ፤ ዶክመንቶቻችን፤ ቪዲዮዎቻችን  በአጠቃላይ ኮምፒዉተራችን ላይ የምንጠቀምባቸዉን መረጃዎች ማከማቻ ነዉ፡፡ ሃርድዲስክ ኤች ዲ ዲ (HDD) እና ኤስ ኤስ ዲ (SSD) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ኤች ዲ ዲ ቀድም ያለ ሲሆን ኤስ ኤስ ዲ ደግሞ እጅግ ዘመናዊ እና ፈጣን መረጃ ማከማቻ ነዉ፡፡ በዋጋ ደረጃም ኤስኤስ ዲ ዉድ ነው፡፡ ከአንድ በላይ ሀርድ ዲስክ በላይ መቀበል በሚችሉ ላፕቶፖች ላይ ሁለቱንም አቀላቅልለን መጠቀም እንችላለን፡፡ ሁለቱም ላለዉ ሰዉ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሲጭን ኤስ ኤስ ዲ ላይ መጫኑ ይመረጣል፡፡ ሃርድ ዲስክ በአብዛኛዉ 250 ጊጋ ባይት ፤ 500 ጊጋ ባይት ፤ 1 ቴራ ባይት እያለ ቢቀጥልም ለመጠነኛ ስራ ከ500 ጊጋ ባይት ጀምሮ ያላቸው ይመከራሉ፡፡ ሃርድ ዲሰክን በቀላሉ መቀየር እና ማሳደግ ይቻላል፡፡

6. ዲዛይን እና ስክሪን ሳይዝ

በጣም ጠቃሚ ከሆኑ መስፈርቶች አንዱ ዲዛይን ነዉ፡፡ በጣም ቀጭን እና ቀላል ክብደት ያላቸዉ ኮምፒዉተሮች ዋጋቸው ከፍ ያለ ነዉ፡፡ እንደ ፈለግንበት ምክንያታችን የምንፈልገዉ ዲዛይን እና ሳይዝ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ለቀላል ስራዎች እና ለሴቶች ለመያዝ ምቹ የሆን አነስተኛ ስክሪን ያላቸዉ ኮምፒዉተሮች ሲመከሩ ፤ ለግራፊክስ ዲዛይነሮች እና ጌመሮች ከፍ ያለ እስክሪን እና ከበድ ያለ ላፕሮቶፖች ይመከራሉ፡፡

ከ14 ኢንች እስክ 15.6 ኢንች ስክሪን ሳይዝ ያላቸዉ ኮምፒዉተሮች በብዛት ገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡

ተች ስክሪን ፤ ስክሪናቸዉ ከቦዲ መላቀቅ የሚችል 360 ዲግሪ መሽከርከር የሚችል አይነት ኮምፒዉተሮችም በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡

7. ኦፕሬቲንግ ሲስተም

ለአንድ ኮምፒዉተር ኦክስጅኑ ኦፕሬቲንግ  ሲስተም ነው፡፡ ላፕሮፓችን ተጭኖበት የመጣበት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ካለ እሱን መመልከት የተሻለ ነዉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለዊንዶዉስ ላይሰንስ የሚያስከፍሉን ግዜ አለ እና በትክክል ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን አብረዉ እንደጫኑልን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ ባለሙያዎች ከሆንን ተጨማሪ እንደ ሊነክስ እና ማክ አይነት ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ሊያስፈልጉን ይችላሉ፡፡

8. ከሽያጭ በኋላ ያለ የጥገና አገልግሎት እና ዋስትና

ላፕቶፕ ስንገዛ አንዱ እና ወሳኙ ነጥብ ከገዛን በኋላ የምናገኘዉ የጥገና አግልግሎት እና ችግር ቢያጋጠመዉ ለደህንነቱ ከሻጫችን የሚሰጠን ዋስትና ነዉ፡፡ ላፕቶፕ ሲበላሽ 2 አይነት ችግሮች ይኖሩታል የመጀመሪያዉ ከእኛ ገዢዎች አያያዝ ክፍተት የሚፈጠር ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ከእቃዉ የጥራት ጉድለት የሚከሰት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ ዋስትና ተግባራዊ የሚደረገው ከእቃዉ የጥራት ጉድለት ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሻጮች ለገዢዎች የአንድ አመት ዋስትና ይሰጣሉ፡፡


Reviews

  Utura Gololcha
 Jun 5, 2023
  "I like it. Incase of it is:- -easy to understood -short and precise and - good view for client. BUT if it is write with English in parenthesis like ኦፕሬቲንግ ሲስተም (Operating System) it help customer to access more information on make confuse him/her."

Post Comment