About this About Book
ደራሲዋ በመገናኛ ብዙኋን ስለ ሀገራችን ሴቶች የላቀ መሪነት፣ ሴቶች በታሪክ፣ በሀይማኖት ስላላቸው ታላቅ ስፍራ እና ክብር፣ የሀገር ስያሜ ተምሳሌትነት ዓየር ላይ ከሚነገረው እና ምድር ላይ ከሚታየው ሴቶች እንደየኑሮ ደረጃ እና አካባቢያቸው ከሚደርስባቸው የተለያዩ ፍረጃዎች እና ጫናዎች ጋር እያነጻጸረች፣ ወደ እራሷ እያየች ኢትዮጵያዊት የፈረንጅ ሚስትስ ቦታዋ የቱ ጋ ይሆን? ከሚል ጥያቄ ተነስታ፣ እስከዛሬ በይፋ ያልተነገሩ የፈረንጅ ሚስት ታሪኮች በግል ገጠመኞቿ አስደግፋ ፣ በግልጽነት እና በድንቅ አተራረክ ሰርሳሪ የሆነ መጽሐፍ ፅፋልናለች፡፡
መጽሐፉ ማኅበረሰቡ በፈረንጅ ሚስት ላይ በግልጽ የሚያሳየው እና የሚሰነዝረው አሉታዊ አስተያየት እኔም በግል ተቋዳሽ ወደ ሆንኩበት ወደ ራሴ ትውስታ መለስ ብዬ እንዳይ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ማኅበረሰብም እራሳችንን እንግዳ ተቀባይ፣ ፈሪሃ ፈጣሪ ያደረብን፣ ለእራሳችን ክብር ያለን ኩሩ ሕዝብ እያልን በአደባባይ እየመሰከርን ድርጊታችን ስለራሳችን ካለን እምነት እጅግ ተቃራኒ የመሆኑን ጉዳይ እንድጠይቅ አድርጎኛል። የፈረንጅ ሚስት መጽሐፍ ሁሉም እራሱን እና ማኅበረሰቡን በአዲስ ዓይን እንዲመለከት የማስገድድ አቅም ያለው ግልጽ ፣ቀላል እና ጥልቅ መጽሐፍ ነው፡፡
አዜብ ወርቁ
Review
5
2 Review
Nuuroo usmaan jobo
Jul 2, 2024
Nuuroo usmaan jobo
chakiso
Dec 25, 2024
wow