About this About Book
መግቢያ
ይህን መጽሐፈ ፍቅር በሚል ርዕስ የቀረበ ጽሑፍ ለመጻፍ ብዙ ዓመት ወስዷል። የጽሁፉ መነሻ ሃሳብ እኔ ወደሰሜን አሜሪካ በስደት ከመጣሁ ወዲህ አላስቀምጥ አላስተኛ እያለ የሚነዘንዘኝን ጥያቄ ሳወጣ ሳወርድ በግሌ ምላሽ ለመስጠት ካደረግሁት ጥረት ጋር ይያያዛል።
መግቢያ ይህን መጽሐፈ ፍቅር በሚል ርዕስ የቀረበ ጽሑፍ ለመጻፍ ብዙ ዓመት ወስዷል። የጽሁፉ መነሻ ሃሳብ እኔ ወደሰሜን አሜሪካ በስደት ከመጣሁ ወዲህ አላስቀምጥ አላስተኛ እያለ የሚነዘንዘኝን ጥያቄ ሳወጣ ሳወርድ በግሌ ምላሽ ለመስጠት ካደረግሁት ጥረት ጋር ይያያዛል።
ከዚህ በተጨማሪ በኖርኩበት ሃገርና አካባቢ ለምሳሌ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን፣በጣሊያን፣ በአሜሪካና በካናዳ እንዲሁም በኤርትራ (የኢትዮጵያ ክፍል በነበረችበት ጊዜ) ባሳለፍኩት ህይወት በትምህርት ቤት፣ በትግል፣በእስር ቤት፣ በስራ ፣ በቤተክርስቲያን ከተለያዩ ሰዎች ጋር በመገናኘትና በመጻሕፍት ሳቢያ ያከማቸሁት እውቀት፣ በተለይም ደግሞ እግዚአብሔር የእድሜ ፀጋ ስለቸረኝ አሁን ወደ ሰባ የዕድሜ ክልል መድረስ በመቻሌ ከህይወት ተሞክሮ ለብዙ ጥያቄዎች መልስ አግኝቻለሁ ብዬ እገምታለሁ። ከነዚህ ጥያቄዎች አንዱና ዋነኛው “የመጨረሻው እውነት የቱ ነው” የሚል ነው። ሌላው ደግሞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በተደጋጋሚ እንደሚታየው መንግሥት በተቀየረ ቁጥር የህዝቡ መከራ እየባሰ እንጅ እየቀነሰ ባለመሄዱ ይህ ለምን ሆነ የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አስገድዶኛል። ይህ መጽሐፍ እንግዲህ የነዚህና ሌሎች ጥያቄዎች ውጤት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለፍቅር ምንነትና ስለማንነቱ ያስረዳል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክነቱን ክብር ትቶ እኛን ለማዳን ከኛ አንዱ ሆኖ ወደምድር በመጣ ጊዜ ያስተማረውና የተገበረው በሙሉ ፍቅርን ነው። በስተመጨረሻም በእንጨት መስቀል ላይ እንኳ የሰቀሉትን በይፋ ይቅር እንዳላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል።